Fana: At a Speed of Life!

የቲቢ ቤተ ሙከራ ማጠናከሪያ ፕሮጀክት ስብሰባውን እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የምሥራቅ፣ መካከለኛው እና ደቡብ አፍሪካ የጤና ማህበረሰብ ግሎባል ፈንድ ክልላዊ የቲቢ ቤተ ሙከራ ማጠናከሪያ ፕሮጀክት 8ኛው የአስተባባሪ ኮሚቴ ስብሰባ እየተካሄደ ነው፡፡

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት÷ በአዲስ አበባ እየተካሄደ የሚገኘው ስብሰባ በፕሮጀክቱ ላይ የሚታዩ ጠንካራ እና ደካማ ጎኖችን ለመገምገም ያለመ ነው፡፡

በፕሮጀክቱ አማካኝነት ኢትዮጵያ ጠንካራ ቲቢ ቤተ ሙከራ አቅም እንዲኖራት የተለያዩ ድጋፎች ማግኘቷ ተገልጿል፡፡

ቲቢን ለመቆጣጠር እና ለማጥፋት እንዲቻል የቲቢ ቤተ ሙከራ ስርዓትን በማጠናከር ረገድ÷ የምሥራቅ፣ መካከለኛው እና ደቡብ አፍሪካ የጤና ማህበረሰብ፣ የዑጋንዳ ሱፐርናሽናል ቤተ ሙከራ እና ግሎባል ፈንድ እንዲሁም ሌሎች አጋሮች ላደረጉት ድጋፍ ዶክተር ሊያ አመስግነዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.