Fana: At a Speed of Life!

አቶ ብናልፍ አንዷለም ኢትዮጵያውያን ለሀገራቸው ሰላም እንዲሰሩ ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ ፣ ጳጉሜን 3 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያውያን ሰላም ለእድገትና ብልጽግና ያለውን ዋጋ በመረዳት ለሀገራቸው ሰላም እንዲሰሩ የሰላም ሚኒስትሩ ብናልፍ አንዷለም ጥሪ አቀረቡ።

ጳጉሜን 3 የሰላም ቀንን አስመልክቶ የሰላም ሚኒስቴር መግለጫ ሰጥቷል፡፡

መግለጫውን የሰጡት ሚኒስትሩ ብናልፍ አንዷለም  እለቱ “ሰላም ለኢትዮጵያ“ በሚል መሪ ቃል የሰላምን ግንዛቤ በሚፈጥሩ የተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል ብለዋል፡፡

ፍላጎታችን ሰላም እና ብልፅግና ነው ያሉት ሚኒስትሩ÷ ይህ እድገት እና ብልፅግና በኢትዮጵያ እንዲረጋገጥ ሰላም ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በመሆኑም መላው ኢትዮጵያውያን የሰላምን ዋጋ በመረዳት ለዚህ በጎ አላማ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲወጡ እና በጋራ ለሀገራቸው ሰላም እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ዜጎች በስጋት እንዲኖሩ እና ተገደን ወደ ጦርነት እንድንገባ የሚያደርጉ ሀይሎችን እናወግዛለን ያሉት ሚኒስትሩ፥ ፀረ ሰላም ሀይሎችን ሁሉም ሊያወግዛቸው ይገባል ብለዋል።

በዓሉን ምክንያት በማድረግ የአምስት ኪሎ ሜትር የእግር ጉዞ እና የሙዚቃ እና የኪነ ጥበብ ስራዎች እንዲሁም የፓናል ውይይት እንደሚደረግ ጠቅሰዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.