Fana: At a Speed of Life!

2 ዞኖች ለመከላከያ ሠራዊት ከ47 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀዲያ እና ደቡብ ጎንደር ዞኖች ለመከላከያ ሠራዊት ከ47 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የአይነት ድጋፍ አደረጉ፡፡

የሀዲያ ዞን ሕዝብና አስተዳደር 42 ሚሊየን 131 ሺህ ብር ብር ግምት ያላቸው÷ 350 ሰንጋ፣ 542 ፍየልና በግ እንዲሁም 1ሺህ 188 ኩንታል ለምግብነት የሚውሉ የኢንዱስትሪ ምርቶችን ጨምሮ 135 ኩንታል ስኳር ድጋፍ ማድረጋቸውን የሀዲያ ዞን ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

በተመሳሳይ የደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደር እና ሕዝብ ለጥምር ጦሩ ከ5 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው ለእርድ የሚሆኑ እንስሳትን ጨምሮ የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.