Fana: At a Speed of Life!

አቶ ሙስጠፌ ሙሃመድ ከአሜሪካ ኮንግረስ የውጭ ግንኙነት ቋሚ ኮሚቴ አባላት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሠ-መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሃመድ ከአሜሪካ ኮንግረስ የውጭ ግንኙነት ቋሚ ኮሚቴ ልዑክና ከአሜሪካ ተራድዖ ድርጅት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በጽኅፈት ቤታቸው ተወያዩ።

ልዑኩ በስቴቨን ሊቦደር የተመራ ሲሆን፥ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ተራድዖ ድርጅት ምክትል ዳይሬክተር የሆኑትን አዳም ስሺምት አካቷል፡፡

የሶማሌ ክልል ርዕሠ-መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ፥ በክልሉ በተከሰተው ድርቅ እና አደጋውን ለመቋቋም የክልሉ መንግሥት እያደረገ ባለው ርብርብ ላይ ለልዑካኑ ገለጻ አድርገውላቸዋል፡፡

በተጨማሪም ርዕሠ-መስተዳድሩ ሽብርተኝነት ለማጥፋትና አሸባሪውን አልሸባብ ለመደምሰስም የሶማሌ ክልል ብሎም ኢትዮጵያ ቁርጠኛ መሆናቸውን ነው የገለጹላቸው፡፡

ልዑካኑም ኢትዮጵያ በተለይም ክልሉ አሸባሪነትን ለመዋጋት እያደረገ ላለው የተጠናከረ ሥራ አድንቆታቸውን ገልጸዋል፡፡

አሜሪካ በጉዳዩ ላይ እገዛ እንደምታደርግ ነው የተናገሩት፡፡

በድርቁ ለተጎዱ ዜጎች ለሚደረገው ቀጣይ ድጋፍም የአሜሪካ ተራድዖ ድርጅት የበለጠ እንዲሳተፍ ጥሪ መቅረቡንም ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.