ኢትዮጰያ የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይን በ10 ዓመት እቅዷ ላይ በማካተት በትኩረት እየሰራች ነው – ዶ/ር ፍጹም አሰፋ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጰያ የአካባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥን በ10 ዓመት እቅዷ ላይ በማካተት በትኩረት እየሰራች መሆኑን የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አሰፋ ገለጹ፡፡
ሚኒስትሯ ከዴንማርክ አምባሳደር ብራሰሚዝ ሲንድ ቢጄርግ እና ከዓለም የሪሶርስ ኢንስቲትዩት የኢትዮጵያ ተወካይ አቶ አክሊሉ ፍቅረ ስላሴ ጋር በአየር ንብረት ለውጥና በልማት እቅዶች ላይ መክረዋል፡፡
በውይይቱ የዴንማርክና የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ትብብር ረዥም ጊዜን ያስቆጠረ መሆኑን ሚኒስትሯ አንስተዋል፡፡
ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚን እየገነባች መሆኗን ተናግረዋል።
የዴንማርክ መንግስትና የዓለም ሪሶርስ ኢንስቲትዩት እያደረጉ ላሉት ድጋፍ ማመስገናቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ኢትዮጵያ ከካርቦን የጸዳ ኢኮኖሚን በአስተማማኝ ሁኔታ ለመገንባት የጀመረችውን ሁሉን አቀፍ ተግባርም አጠናክራ እንደምትቀትል ዶክተር ፍጹም አሰፋ አረጋግጠዋል፡፡
የዓለም የሪሶርስ ኢንስቲትዩት የኢትዮጵያ ተወካይ አቶ አክሊሉ ፍቅረ ስላሴ ፥ በአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖዎችና የአካባቢ ተጽዕኖን በተመለከተ ጥናት ለማድረገ፣ በቴክኒክና አቅም ግንባታ ለማገዝ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!