Fana: At a Speed of Life!

“የትራንስፖርት ችግሩን የሚያቀሉ አውቶብሶችን ይዘን እንኳን አደረሳችሁ ስንል ደስታ ይሰማናል” – ከንቲባ አዳነች አበቤ

 

አዲስ አበባ፣ ጷጉሜን 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአገልጋይነት ቀን በትራንስፖርት አገልግሎት የሚደርሰውን እንግልት ለማቃለል ዘመናዊ አውቶብሶችን ይዘን እንኳን አደረሳችሁ ስንል ደስታ ይሰማናል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አበቤ ገለጹ፡፡

አስተዳደሩ ከዓለም ባንክ በተገኘ ብድር የተገዙ 110 ዘመናዊ አውቶቡሶችን ዛሬ ሥራ አስጀምሯል ።

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ አውቶቡሶቹን ሥራ ባስጀመሩበት ወቅት ባደረጉት ንግግር÷ አውቶቡሶቹ በ16 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ወጪ ከዩ ቲ ቶንግ ኩባንያ የተገዙ ናቸው፡፡

አዎቶቡሶቹ በከተማዋ እየጨመረ የመጣውን የትራንስፖርት ችግር ለማቃለል እንደሚያግዙ ጠቁመው÷ በተለይም የስመ ጥሩውን እና ዕድሜ ጠገቡን የአንበሳ አውቶቡስ ብራንድ እንደያዙ ይንቀሳቀሳሉ ብለዋል ።

በተጨማሪም የከተማ አስተዳደሩ በቀጣዮቹ ሦስት ወራት 200 አውቶብሶችን ወደ ሥራ እንደሚያስገባ ከንቲባ አዳነች ተናግረዋል።

አስተዳደሩ ዛሬ ወደ አገልግሎት የገቡትን አውቶብሶች ጨምሮ መንግሥት ዘርፉን ለማዘመን በቁርጠኝነት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በታሪኩ ለገሰ እና በመሳፍንት እያዩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.