Fana: At a Speed of Life!

የዌልሱ ልዑል ቻርለስ የእንግሊዝ ንጉሥ ሆኑ

አዲስ አበባ ፣ ጳጉሜን 4 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዌልሱ ልዑል ቻርለስ የእንግሊዝ ንጉስ ሆኑ።

ልዑሉ የንግስት ኤልሳቤጥ 2ኛ ህልፈትን ተከትሎ የእንግሊዝ 40ኛው ንጉስ መሆናቸውን ቢቢሲ አስነብቧል።

የሀገሪቱ የንግስና ሂደት ከተከናወነ በኋላ ልዑሉ በይፋ ንግስናውን ተቀብለው ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ንግስት ኤልሳቤጥ 2ኛ በትናንትናው እለት በ96 አመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ይታወሳል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.