Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮ – ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ በተለያዩ ስፖርታዊ ውድድሮች የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ስፖርተኞች የማበረታቻ ሽልማት አበርክቷል።   

በስካይ ላይት ሆቴል በተካሄደው የሽልማት መርሐ ግብር ላይ አመርቂ ውጤት ላስመዘገቡ ስፖርተኞች እንዳስመዘገቡት ውጤት ከአምስት ሺህ እስከ 300 ሺህ ብር የሚደርስ የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

የኢትዮ – ኤሌክትሪክ አትሌት የሆነችውና በ18ኛው የኦሪገን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶች ማራቶን ለሀገሯ የወርቅ ሜዳልያ ያስገኘችው ጎቲቶም ገብረስላሴ ልዩ ተሸላሚ በመሆን የ300 ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቶላታል።

ክለቡ በ2014 ዓ.ም የውድድር ዘመን በአትሌቲክስ፣ በሴቶች እግር ኳስ፣ በብስክሌት እና በጠረጴዛ ቴኒስ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ስፖርተኞች የገንዘብና የምስክር ወረቀት አበርክቷል፡፡

በሽልማት ስነ ስርዓቱ የኢትዮ – ኤሌክትሪክ ክለብ ፕሬዚዳንት አቶ ጫላ እና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ መገኘታቸውን ከክለቡ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.