Fana: At a Speed of Life!

አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ለ200 አቅመ ደካሞች ማዕድ አጋሩ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ የአገልጋይነት ቀንን ምክንያት በማድረግ 200 ለሚደርሱ አቅመ ደካሞች ማዕድ አጋርተዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ጊዜ እንደተናገሩት÷ ማዕድ ማጋራትና መረዳዳት የኢትዮጵያውያን የቆየ እሴት በመሆኑ እርስ በእርስ በመደጋገፍ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በጋራ መቅረፍ ይገባል፡፡

አንድነታችንን በመጠበቅ ለችግሮቻችን የጋራ መፍትሄ ማምጣት ከሁሉም የሚጠበቅ እንደሆነም ተናግረዋል ።

አዲሱ አመት የሰላም፣ የፍቅር እና የብልጽግና እንዲሆን ለመላው ኢትዮጵያውያን ምኞታቸውን መግለጻቸውን ከጋምቤላ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.