Fana: At a Speed of Life!

አዲሱን ዓመት በጦርነቱ ምክንያት የተፈናቀሉትን መልሶ በማቋቋም ማክበር ይገባል – ም/ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲሱን ዓመት ስናከብር የተቸገሩትን በመርዳት እና በጦርነቱ ምክንያት የተፈናቀሉትን መልሶ በማቋቋም መሆን እንዳለበት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ ገለጹ፡፡
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግሥት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ ለአዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመልዕክታቸውም አዲሱ ዓመት የጀመርናቸው የልማት፣ የሰላምና የመልካም አስተዳደር ሥራዎችን በተጨባጭ በተግባር ፈጽመን ሕዝቡ የሚጠይቃቸውን ጥያቄዎች መመለስ የምንችልበት እንደክልል ብሎም እንደሀገር እየተፈታተኑን ያሉ የሰላም ዕጦት ችግሮችን የምንፈታበት ዘመን እንዲሆን እመኛሁ ብለዋል፡፡
የአሸባሪው ህወሓት ቡድን በሀገራችን ላይ ያወጀውን ጦርነት ለመመከት የክልላችን ሕዝብ በግንባርና በደጀን የሚደረገውን ተልዕኮ ለመወጣት እያሳየ ያለው ቁርጠኝነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡
የሚታዩ የፀጥታ ስጋቶችን በንቃት በመጠበቅ በጦርነቱ ሳቢያ ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች በማቋቋም እንዲሁም የግንባርና የደጀንነት ድጋፍ በመስጠት ሁሉም የክልሉ ሕዝብ አስተዋጽዖ እንዲያበረክት ጥሪ አቅርበዋል፡፡
አዲሱ ዓመት የተቸገሩትን በመርዳት በጦርነቱ ምክንያት ከቤት ንብረት የተፈናቀሉትን መልሶ በማቋቋም ሊከበር ይገባል ብለዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.