Fana: At a Speed of Life!

ከመተከል እና አዊ ዞኖች የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀደመ ቦታቸው ለመመለስ ያለመ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣መጋቢት 8፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአማራና የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በመተከል እና አዊ ዞኖች የተፈናቀሉ የአማራና የጉሙዝ ማህብረሰብ አባላትን ወደ ቀደመ ቀያቸው መመለስ በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።

በውይይት መድረኩ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገ ጥሩነህ እና የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰንን ጨምሮ ከሁለቱ ክልሎች የተውጣጡ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

ውይይቱ በቤንሻንጉል ክልል መተከል ዞን እና በአማራ ክልል አዊ ዞን የተፈናቀሉ የአማራ እና የቤንሻንጉል ማህበረሰብ አባላትን ወደ ቀደመ ቦታቸው ለመመለስ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

ከዚህ ባለፈም የሁለቱን ክልሎች ህዝቦች ሰላም በዘላቂነት ማስከበር በሚቻልበት ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸው ተመላክቷል።

በናትናኤል ጥጋቡ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.