Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ክልል ለ1 ሺህ 445 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ጳጉሜን 5 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል መንግስት አዲሱን አመት ምክንያት በማድረግ ለ1 ሺህ 445 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን የክልሉ ፍትህ ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ሃላፊ አቶ ሶፎንያስ ደስታ የክልሉ ይቅርታ ቦርድ በደንቡና መምሪያው መሰረት ለርዕሰ መስተዳድሩ ባቀረበው ዝርዝር መሰረት በክልሉ ከሚገኙ 15 ማረሚያ ተቋማት የተቀመጠውን መስፈርት የሚያሟሉ መለየታቸውን ገልጸዋል።

በዚህ መሰረት መስፈርቱን በማሟላት ይሁንታ ያገኙ 1 ሺህ 445 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ ተደርጎላቸዋል ብለዋል።

በተጨማሪም 21 የህግ ታራሚዎች ደግሞ የእስራት ዕድሜ እንደተቀነሰላቸው ኢዜአ ዘግቧል።
ይቅርታ የተደረገላቸው በአግባቡ የታረሙ፣ የባህሪ ለውጥ ያመጡ፣ ትምህርትና ምክር የወሰዱ፣ መሻሻላቸው የተረጋገጠ፣ የፍርድ ጊዜያቸውን አንድ ሁለተኛና አንድ ሶስተኛ ያጠናቀቁ፣ ከበደሉት ግለሰብ ጋር የታረቁና ካሳ የከፈሉ ናቸው ብለዋል፡፡

ይቅርታው ከነገ መስከረም 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የሚተገበር መሆኑን ጠቁመዋል።

በድምሩም በመጀመሪያው ዙር የ2015 የይቅርታ መርሐ ግብር 1 ሺህ 466 ታራሚዎች የይቅርታና እስራት ጊዜ ቅናሽ ተጠቃሚ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.