Fana: At a Speed of Life!

የአንድነት ቀን በኢፌዴሪ አየር ኃይል ተከበረ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “ስናብር ስናምር” በሚል መሪ ቃል የአንድነት ቀን በኢፌዴሪ አየር ኃይል በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል።
 
በመርሐ ግብሩ የተገኙት የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ይልማ መርዳሳ እንደተናገሩት÷አየር ሃይል የሰላም ቋንቋ የማይገባቸው አሸባሪዎች የከፈቱብንን ጦርነት ለመመከት ዝግጁ ነው።
 
የውስጥ አሸባሪዎችን ለማገዝ የኢትዮጵያን አየር ክልል ያለፍቃድ ጥሶ ለመግባት የሚሞክሩ የውጭ ጠላቶቻችን እንዳመጣጣቸው ለማስተናገድ አየር ኃይላችን ከመቼውም ጊዜ በላይ በሙሉ ዝግጁነት ላይ ይገኛል ነው ያሉት፡፡
የቢሾፍቱ ከተማ ከንቲባ አቶ አለማየሁ አሰፋ በበኩላቸው ÷ ጠላት ሊያንበረክከን ያልቻለው በአንድነት በማበር ስለምንሰራ መሆኑን የኋላ ታሪካችን ይናገራል ብለዋል።
 
በእለቱ ለጀግኖች የሰማዕታት ቤተሰቦች የገንዘብ ድጋፍ መደረጉንም ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.