የድሬዳዋ አስተዳደር በአፋር ለሚገኙ መከላከያ ሰራዊት የቁም እንስሳቶችን ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ አስተዳደር በአፋር ግንባር ጭፍራ ለሚገኙ መከላከያ ሰራዊት ለበዓል የቁም እንስሳቶችን ድጋፍ አደረገ ፡፡
የድሬዳዋ ከንቲባ ከድር ጁሃር፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት ተጠሪና የድሬዳዋ አስተዳደር ብልፅግና ፅ/ቤት ሀላፊ ኢብራሂም ዩሱፎ ፣የብልፅግና ፅ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ደረጀ ፀጋዬ እና ሌሎች የአስተዳደሩ የስራ ሀላፊዎች በጋራ በመሆን ነው ለአባላቱ የቁም እንስሳቶችን ድጋፍ ያደረጉት።