Fana: At a Speed of Life!

በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ የኢፌዴሪ ኤምባሲዎችና ቆንስላዎች አዲሱን ዓመት አከበሩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች እና ቁንስላ ጽኅፈት ቤቶች አዲሱን ዓመት በደማቅ ሥነ-ሥርዓት አክብረዋል፡፡

በጅዳ የሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽኅፈት ቤት፣ በሕንድ ፣ በደቡብ ሱዳን ፣ በጂቡቲ፣ በሞሮኮ፣ በአቡዳቢ፣ በፈረንሳይ ፣ ሮም ፣ እንግሊዝ ፣ ኩዌት ፣ብራሰልስ ፣ናይጄሪያ ፣ደቡብ ኮርያ እንዲሁም በሌሎች ሀገራት የሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች አዲሱን ዓመት በደማቅ ሥነ-ሥርዓት አክብረዋል፡፡

ኤምባሲዎቹ እና ቆንስላዎቹ ከትናንት ጀምሮ የተለያዩ የሃይማኖት መሪዎች፣ አምባሳደሮች፣ የሥራ አመራሮች፣ ጥሪ የተደረገላቸው ተጋባዥ እንግዶች እንዲሁም ዲፕሎማቶች አዲሱን ዓመት እና የአንድነት ቀንን ምክንያት በማድረግ መሰባሰባቸው ነው የተገለጸው፡፡

ባለፉት ጥቂት ዓመታት በኢትዮጵያ አንድነት፣ ሠላም እና ብልጽግና ላይ የተቃጡ በርካታ ሙከራዎች ማለፋቸውን የኤምባሲዎቹ አምባሳደሮች በንግግራቸው ዳሰዋል፡፡

ኢትዮጵያ እነዚህን ፈታኝ ሁኔታዎች ተቋቁማ በበርካታ ዘርፎች ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ መልኩ አንጸባራቂ ድሎችን ማስመዝገቧንም ነው ያወሱት።

ኤምባሲዎቹ እና ቆንስላዎቹ ለኢትዮጵያ አንድነት፣ ሉዓላዊነትና ክብር ያላቸውን ቁርጠኝነትም ማረጋገጣቸውን በየሀገራቱ ከሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች እና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በሀገር ቤት ለሚገኙ ኢትዮጵያውያንም የእንኳን ለ2015 የዘመን መለወጫ ዓመተ-በዓል አደረሳችሁ የሚል መልዕክቶቻቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.