አምባሳደር ባጫ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የደስታ መግለጫን ለዊሊያም ሩቶ አደረሱ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ባጫ ደበሌ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለኬንያው አዲስ ተመራጭ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ያስተላለፉትን የደስታ መግለጫ አደረሱ።
ኢትዮጵያ እና ኬንያ በጋራ መስራታቸውን እንደሚቀጥሉ አምባሳደሩ ገልዋል።
በተለይም በልማት፣ ቀጠናዊ ሠላም እና ፀጥታ በማስፈን እንዲሁም በኢኮኖሚያዊ ትሥሥር ሀገራቱ ተቀራርበው መሥራታቸውን እንደሚቀጥሉ አምባሳደር ባጫ በትዊተር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት አመላክተዋል።