Fana: At a Speed of Life!

አቶ ሙስጠፌ ከክልሉ ልዩ ሃይልና መከላከያ ሠራዊት አባላት ጋር አዲስ ዓመትን አከበሩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ የተመራው የክልሉ ከፍተኛ የመንግስትና የፀጥታ አመራሮች ልዑክ ከክልሉ ልዩ ሃይልና ከመከላከያ ሠራዊት አባላት ጋር አዲስ ዓመትን አከበሩ፡፡

ልዑኩ በኢትዮጵያና በሶማሊያ ድንበር የምትገኘው ኣቶ ከተማ ከሚገኙ የሶማሌ ክልል ልዩ ሀይልና የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ጋር ነው አዲሱን ዓመትን ያከበሩት።

በመርሐ ግብሩ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድን ጨምሮ ም/ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ኡስማንን፣ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ አያን አብዲ፣ የሶማሌ ልዩ ሀይልና የሀገር መከላከያ ሠራዊት አዛዦች እንዲሁም ሌሎች አመራሮችተገኝተዋል።

ልዑኩ ከክልሉ ልዩ ሀይል ሰራዊትና የመከላከያ ሠራዊት አባላት፣ በኣቶ አካባቢ የሚኖሩ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶችና እናቶች ጋር መወያየታቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

መንግሥት አከባቢውንና ህዝቡን ከሽብርተኛው የአልሸባብ ታጣቂ ቡድን ለመጠበቅ እየወሰደ ያለው እርምጃዎች እንደሚደግፉና ከሰራዊቱ ጎን እንደሆኑ ገልፀው፣ በአከባቢው የልማት ሥራዎች እንዲሰራላቸው ጠይቀዋል።

አቶ ሙስጠፌ ህዝቡን የልማት ተቋዳሽ ለማድረግ መንግሥት እየሰራ እንደሚገኝ ጠቁመው ፥ በሰፍራው ለሚገኘው ሠራዊትም ልዩ ትኩረት እንሰጣለን ብለዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.