ዓለምአቀፋዊ ዜና

ኢራን የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት 85 ሺህ ታራሚዎችን ፈታች

By Tibebu Kebede

March 17, 2020

አዲስ አበባ መጋቢት 8፣ 201 2(ኤፍ ቢ ሲ) የኢራን መንግስት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት 85 ሺህ የሚሆኑ ታራሚዎችን  መፍታቱ ተሰምቷል።

በአሁኑ ወቅት የዓለም ስጋት የሆነውን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመቆጣጠር ሀገራት የተለያዩ እርምጃዎችን እወሰዱ ይገኛሉ።

በዚህ መሰረትም በርካታ ሀገራት ዓለም አቀፍ በረራዎችን ከማገድ እና ድንበራቸውን ከመዝጋታ ባለፈ ዜጎች ለተወሰኑ ቀናት በመኖሪያ ቤታቸው እንዲቆዩ ውሳኔ አስተላልፈዋል።

የኢራን መንግስትም የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት 85 ሺህ የሚሆኑ ታራሚዎች  ከእስር መፍታቱን አስታውቋል።

የእድሉ ተጠቃሚዎች  ከአምስት ዓመት በታች የእስር  ውሳኔ ተላልፎባቸው የነበሩና  በተቃውሞ ሰልፎች ላይ  ተሳታፊ የነበሩ መሆናቸውን የሀገሪቱ ዓቃቤ ህግ አስታውቋል።

በኢራን በኮሮና ቫይረስ እስካሁን 853 ሰዎች ለህልፈት ሲዳረጉ፥ 15 ሺህ የሚደርሱ ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተይዘዋል።

ምንጭ፦https://news.sky.com