Fana: At a Speed of Life!

አየር መንገዱ ባለ 5 ኮከብ ሆቴል ከፈተ 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል መክፈቱን አስታወቀ፡፡

ሆቴሉ ከመንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል -ሁለት ጋር የተገናኘና ለመሳፈሪያ በሮችም  ቅርብ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የሆቴሉ ግንባታ በፈረንጆቹ 2020 ታህሳስ ወር ላይ የተጀመረ ሲሆን ÷ ግንባታው ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት መደረጉ ተመላክቷል፡፡

ሆቴሉ በውስጡ 41 የእንግዳ ማረፊያ ክፍሎች እንዳሉትም ነው የተገለጸው፡፡

ሆቴሉ በስካይላይት ሆቴል ሥር የሚተዳደር መሆኑንም ከአየር መንገዱ  ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.