Fana: At a Speed of Life!

ዘንድሮ ከአንደኛ እስከ ስምንተኛ ክፍል አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ተግባራዊ ይደረጋል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዘንድሮ ከአንደኛ እስከ ስምንተኛ ክፍል አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ተግባራዊ እንደሚደረግ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታው ዶክተር ፋንታ ማንደፍሮ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ እንዳሉት÷ ዘንድሮ አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ተግባራዊ መደረግ ይጀምራል፡፡

እንደ ዶክተር ፋንታ ገለጻ÷ስርዓተ ትምህርቱ ከሀገር በቀል እውቀት ጀምሮ ፣የግብረ ገብነት ፣ የሙያ እና መሰል ከዚህ ቀደም ከነበረው ሥርዓተ ትምህርት የተለዩ የትምህርት አይነቶችና አሰጣጦችን የያዘ ነው።

አዲሱ ስርዓተ ትምህርትን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስፈልጉ ቅድመ ዝግጅቶች መደረጋቸውንም ሚኒስትር ዲኤታው ገልጸዋል።

እስከ መስከረም 9 ቀን 2015ዓ.ም ባሉት ቀናት ውስጥም መምህራን ከአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ጋር ትውውቅ የሚያደርጉበት ስልጠና አንደሚሰጣቸው ተገልጿል፡፡

በትምህርት ዘመኑ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የሚያስችሉ አዳዲስ አሰራሮች እንደሚተገበሩም ታውቋል፡፡

በዙፋን ካሳሁን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.