የጎርፍ አደጋ የእናትና ልጅን ሕይወት ቀጠፈ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ሸዋ ዞን መርሐቤቴ ወረዳ እናትና ልጅ ወንዝ ሲያቋርጡ በጎርፍ አደጋ ህይወታቸው ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ።
እናትና ልጅ በወረዳው ኮራ ወንጭት ቀበሌ ደብረ ወግሽ አካባቢ ነዋሪ መሆናቸው ታውቋል።
የመርሐቤቴ ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት የኮሙኒኬሽን ሚዲያ ክፍል ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር የሻለም እንደሻው እንደገለጹት÷ እናትና ልጅ የግብርና ሥራቸውን ሲከውኑ ውለው ወደ ቤት በመመለስ ላይ ሳሉ ነው በጎርፍ የተወሰዱት፡፡
ወይዘሮ ደፍጦ ጎልቦ ከአምስት ዓመት ልጃቸው አቢቲ አስፋው ጋር ትናንት አረም ሲያርሙ ውለው ወደ ቤታቸው በመመለስ ላይ ሳሉ በጣለው ከፍተኛ ዝናብ ምክንያት በተከሰተ ጎርፍ ወንዙን ለመሻገር ሲሞክሩ ሕይወታቸው ማለፉን ገልጸዋል።