Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የአፍሪካውያን ችግሮች በአፍሪካውያን እንደሚፈቱ የጸና እምነት አላት- አምባሳደር ተሾመ ቶጋ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የአፍሪካውያን ችግሮች በአፍሪካውያን እንደሚፈቱ የጸና እምነት እንዳላት በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተሾመ ቶጋ አስገነዘቡ፡፡

አምባሳደሩ ቤጂንግ ለሚገኙ የአፍሪካ ሕብረት የሰላምና ጸጥታ ምክር ቤት አባላት እና በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተለዋጭ አባል በመሆን እያገለገሉ ለሚገኙ የአፍሪካ ሀገራት አምባሳደሮች በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡

አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ባደረጉት ገለጻ÷ በሰሜን ኢትዮጵያ በአሸባሪው ህወሓት አማካኝነት የተፈጠረውን ግጭት መንግሥት በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ያላሰለሰ ጥረት እያደረገ መሆኑን በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ የአፍሪካውያን ችግሮች በአፍሪካውያን እንደሚፈቱ የጸና እምነት እንዳላት አስገንዝበው÷ በአፍሪካ ሕብረት አማካኝነት ለሚደረገው የሰላም ድርድር ሂደት ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡

አፍሪካውያን እጅ ለእጅ ተያይዘን በአንድነትና በትብብር ከሠራን የሚያጋጥሙንን ችግሮች በቀላሉ መቅረፍ እንችላለን ብለዋል፡፡

አምባሳደሮቹ በበኩላቸው÷ የኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸው ለዚህም ከኢትዮጵያ ጎን እንደሚቆሙ አረጋግጠዋል።

ለአፍሪካዊ ችግር አፍሪካዊ መፍትሔ የሚለው መርህ ወሳኝ ነው ማለታቸውንም በቤጂንግ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.