Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል በሲሚንቶ ምርት ግብይት ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት ያለመ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ በሲሚንቶ ምርት አቅርቦትና ስርጭት ዙሪያ ከሲሚንቶ አምራች ፋብሪካ የሥራ ሃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡

ውይይቱ የሲሚንቶ ምርት ግብይት ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በጋራ እየፈቱ ፍትሃዊ የሲሚንቶ ግብይት እንዲኖር ለማስቻል ያለመ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ከፍተኛ የሰው ሃይል የሚያስተናግደው የግንባታው ዘርፍ እና በዚሁ መስክ የተሰማሩ ሰራተኞች ከስራ ውጭ እንዳይሆኑ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ምክክር ተደርጓል፡፡

ከዚህ ባለፈም በአማራ ክልል በጦርነት ምክንያት ብዙ የመንግስትና የግል ተቋማት የወደሙ በመሆኑ እነዚህን ተቋማት መልሶ መገንባት ታሳቢ ያደረገ የሲሚንቶ ምርት አቅርቦት መኖር እንዳለበት ተነስቷል፡፡

በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች በሲሚንቶ ምርት ስርጭትና ግብይት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን እየገመገሙና እየፈቱ መስራት እንደሚገባቸው መጠቆሙን ከክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.