አምባሳደር ስለሺ ከተመድ የአየር ንብረት ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስለሺ በቀለ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ኢንገር አንደርሰን ጋር ተወያዩ፡፡
አምባሳደር ስለሺ በኢትዮጵያ እየተከናወነ የሚገኘውን የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በተመለከተ ለዋና ዳይሬክተሯ ገለጻ አድርገዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም በኢትዮጵያ የስንዴ ልማት እያስገኘ ያለውን ውጤት እና በሌሎች ስኬታም የልማት ስራዎች ላይ ማብራሪያ መስጠታቸውን ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢንገር አንደርሰን በበኩላቸው፥ በተመድ የአየር ንብረት ፕሮግራም ኢትዮጵያ በአካባቢ ጥበቃ እያከናወነቻቸው በሚገኙ ስራዎች እና በሌሎች የልማት ጉዳዮች ላይ በትብብር መስራቱን እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡