Fana: At a Speed of Life!

የዓለም ጤና ድርጅት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሊያገረሽ እንደሚችል አስጠነቀቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ጤና ድርጅት በኮቪድ-19 ስርጭት የሚሞቱት ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ ቢመጣም ዳግም ሊያገረሽ እንደሚችል አስጠነቀቀ።

ድርጅቱ ወደፊት የኮሮና ቫይረስ ሊያገረሽ እንደሚችል በመጥቀስ፥ ሀገራት ሊፈጠሩ ለሚችሉ ሁኔታዎች ሁሉ ነቅተው በመጠበቅ ዝግጁ እንዲሆኑም አሳስቧል።

እንደ ድርጅቱ መረጃ ከፈረንጆቹ መስከረም 5 እስከ 11 ባለው ሳምንት በዓለም ዙሪያ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ካለፈው ሳምንት ጋር ሲነፃፀር በ28 በመቶ ቀንሷል።

በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥርም ካለፈው ሳምንት አንጻር በ22 በመቶ መቀነሱንም ነው ያመላከተው፡፡

ድርጅቱ በመግለጫው ወረርሽኙን ለመግታት ይበልጥ መፍጠንና መጠንከር የሚገባን ጊዜ ላይ ነን ብሏል፡፡

ቫይረሱ በአሁኑ ጊዜ በዓለም ዙሪያ በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰራጨ መሆኑን የጠቆሙት ደግሞ የዓለም ጤና ድርጅት የድንገተኛ አደጋ ፕሮግራም ቴክኒካል መሪ ማሪያ ቫን ኬርሆቭ ናቸው።

ይሁን እንጅ የስርጭቱ መጠን ለድርጅቱ ሪፖርት ከሚደረገው ቁጥር ጋር ሲነጻጸር አነስተኛ መሆኑን ጠቅሰዋል።

እንደ እርሳቸው ገለጻ ቫይረሱ ዓለም ላይ ሪፖርት ከሚደረገው ቁጥር በበለጠ ሁኔታ እየተዛመተ ይገኛል።

ከዚህ አንጻርም ሀገራት እና ዜጎች ተገቢውን ዝግጅት እና ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል ማለታቸውን ሺንዋ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.