Fana: At a Speed of Life!

በቡና የወጪ ንግድ ስኬት አስተዋጽዖ ላበረከቱ አካላት የዕውቅና ሥነ ስርዓት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በቡና የወጪ ንግድ በተመዘገበው ስኬት አስተዋጽዖ ላበረከቱ አካላት የዕውቅና ሥነ ስርዓት ተካሄደ፡፡

‘’ቡናችን ለአብሮነታች እና ለብልፅግናችን’’ በሚል ርዕስ የኢትዮጵያ ቡና ቀን እየተከበረ ይገኛል፡፡

በመርሐ ግብሩ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ፣ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት መዓዛ አሸናፊ፣ የግብርና ሚኒስትር ዑመር ሁሴን፣ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ደስታ ሌዳሞ ተገኝተዋል።

የግብር ሚኒስትሩ አቶ ኡመር ሁሴን እንዳሉት ፥ ኢትዮጵያ የተሻሻለ የግብርና ፓሊሲ በመቅረፅ በተለይም የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ የስራ እድል መፍጠር፣ ከውጭ የሚገቡትን በማስቀረት በሀገር ውስጥ መተካትና የውጪ ምንዛሬ ለማግኘት እየተሰራ ነው፡፡

ከእነዚህም ውስጥ ቡና ለሀገር የውጪ ምንዛሬ በማስገኘት ውጤታማ ሆኗል ያሉ ሲሆን፥ በቡናው ዘርፍ ላይ የነበረውን የግብይት ሰንሰለት በመበጠስ የዘርፉ ተዋናዮች ተጠቃሚ አድርጓልም ነው ያሉት፡፡

ይህም በሌሎች የግብርና ዘርፎች ላይ በመተግበር ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ ውጤታማ እንድትሆን እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

አትዮጵያ ለውጪ ገበያ በ2014 ዓ.ም 300 ሺህ ቶን ቡና በመላክ 1 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር አግኝታለች ብለዋል የቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶር አዱኛ ደበላ።

አርሶ አደሩን ጨምሮ በዘርፉ የተሰማሩትን በቀጥታ ተጠቃሚ የሚያደርጉ የግብይት አማራጮች መተግብሩና ጤናማ የግብይት ስርዓት እንዲኖር መደረጉ ለውጤታማነቱ እንደምክንያት ይነሳል ተብሏል።

ተግባራዊ የተደረገው የቡና ሪፎርም በዘርፉ የተሰማሩትን በሚስማማቸው የግብይት አማራጭ መገበያየት የሚችሉበት አሰራር እውን እንዲሆን ያስቻለ እንደሆነም ነው የተገለጸው፡፡

የቀጥታ ትስስር ግብይት አርሶአደሩን፣ አልሚውን ፣ አቅራቢውን ሆነ ላኪውን ተጠቃሚ አድርጓልም ተብሏል፡፡

በዛሬው ስነ ስርዓት በቡናው ዘርፍ ላይ ውጤታማነቱ ሚናቸው ከፍትኛ ለሆኑ አርሶ አደሮች፣ አልሚዎች፣ አቅራቢዎች እና ላኪዎች ከፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ሽልማት ተቀብለዋል።

በተለያዩ ዘርፎች የላቀ አበርክቶና አፈጻጸም ነበራቸው ተብሎ ከተሸለሙት  አካለት መካከልም፥ ሚድሮክ ኢንቨሰትመንት ግሩፕ በአምስት የተለያዩ ዘርፎች የዋንጫ ፣ ሜዳሊያ እና ሰርተፍኬት ተብርክቶለታል።

በቅድስት ተስፋዬ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.