ስፓርት

ፌዴሬሽኑ የአሰልጣኝ ውበቱ አባተን ውል አራዘመ

By Feven Bishaw

September 15, 2022

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ውላቸውን ለማራዘም ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር ዛሬ ስምምነት ፈፅመዋል።

አሰልጣኙ ውላቸው መጠናቀቁ የተገለፀ ሲሆን ÷ይህን ተከትሎም ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት በዋና አሰልጣኝነት እንዲቀጥሉ ስምምነት መፈፀሙ ታውቋል፡፡

አሰልጣኝ ውበቱ በ2013 ዓ.ም ብሔራዊ ቡድኑን በመረከብ ያለፉትን ሁለት ዓመታት በስራ ላይ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡

በቆይታቸውም ብሔራዊ ቡድኑ ከስምንት ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ የተመለሰ መሆኑና በቅርቡ ደግሞ ከስድስት ዓመት ቆይታ በኋላ ለአፍሪካ ሀገራት ቻምፒዮንሺፕ (ቻን) የውድድር ተሳትፎ ማሳካቱ መገለፁን ከፌዴሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡