Fana: At a Speed of Life!

በቻይና ህይወት ወደቀደመው ሁኔታ እየተመለሰ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቻይና የኮሮና ቫይረስ ስርጭት እየቀነሰ መምጣቱን ተከትሎ በሀገሪቱ መደበኛ እንቅስቃሴ ወደ ነበረበት ሁኔታ እየተመለሰ መሆኑ ተነግሯል።

የቻይና መንግስት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ባለፉት ሁለት ወራት ዜጎች ቤት ውስጥ እንዲቆዩ ትዕዛዝ ማስተላለፉ ይታወሳል።

ይህን ተከትሎም በሃገሪቱ የተለመደው መደበኛ እንቅስቃሴና የህይዎት ዘይቤ ተቀይሮ እንቅስቃሴዎች ተገድበው ሰዎች በየቤታቸው መቆየት ግድ ብሏቸው ነበር።

አሁን ላይ ግን ሀገሪቱ የኮሮና ቫይረስን ለመቀነስ እና ለመቆጣጠር ያደረገችው ጥረት ፍሬ ማፍራቱን ተከትሎ መደበኛ የህይወት እንቅስቃሴ ወደ ተለመደው እየተመለሰ ነው ተብሏል።

ላለፉት ሁለት ወራት የተሰማሩበትን አሳ የማጥመድ ተግባር ሳይፈፅሙ የቆዩት ያንግ፥ ያለፉት ሁለት ወራቶች ያልተለመዱ እንደነበሩ ተናግረዋል።

ያንግ ከቫይረሱ መከሰት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ አሳ ወደ ማጥመድ መመለሳቸውን በመጥቀስ ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የሁቤይ ግዛትን የምትዋሰነው ቾግቺንግ በቫይረሱ የተያዙ 500 ሰዎች የተገኙባት ሲሆን አሁን ላይ መንግስት እያደረገ ባለው ቁጥጥር ነዋሪዎቿ ወደ ተለመደው የህይወት ዘይቤ እየተመለሱ ነው ተብሏል።

ከቻይና 34 ግዛቶች መካከል በ13 ግዛቶች በቫይረሱ ከተያዙ 81 ሺህ ሰዎች ውስጥ 69 ሺህዎቹ ከቫይረሱ አገግመዋል።

ምንጭ፦ አልጀዚራ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.