Fana: At a Speed of Life!

ሚኒስትሮቹ የጂቡቲ ኢነርጂ ሚኒስትር ዮኒስ አሊ ጉዲን በጽህፈት ቤታቸው አነጋገሩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ እና የገንዝብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ከጂቡቲ ኢነርጂ ሚኒስትር ዮኒስ አሊ ጉዲ ጋር ተወያዩ፡፡

የኢፌዴሪ የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ፥ ከጂቡቲ ኢነርጂ ሚኒስትር ዮኒስ አሊ ጉዲ ጋር በማዕድን ኢነርጂ ዘርፍ ልማት ዙሪያ በትብብር መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

በተመሳሳይ የገንዝብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ከጂቡቲ ኢነርጂ ሚኒስትር ዮኒስ አሊ ጉዲ በሁለትዮሽ እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ሚኒስትሮቹ በሁለቱ ሀገራት ለመተግበር የታቀዱ ፕሮጀክቶች የደረሱበትን ሒደት መገምገማቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.