Fana: At a Speed of Life!

መድሃኒት የተላመደ የቲቢ በሽታን ለመቆጣጠር ውጤታማ ስራ ተሰርቷል – ጤና ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) መድሃኒት የተላመደ የቲቢ በሽታን ለመቆጣጠር የተሰሩ ተግባራት ውጤት ማስገኘታቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የጤና ሚኒስቴር የበሽታዎች መከላከል ዳይሬክቶሬት ዓመታዊ የቲቢና የሥጋ ደዌ መርሐ ግብር የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ተካሂዷል፡፡

በሚኒስቴሩ የፕሮግራም ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ያደታ ባደረጉት ንግግር፥ የጤና ሚኒስቴር በሽታዎችን በመከላከል ረገድ ትኩረት ሰጥቶ ውጤታማ ሥራ መስራቱን አብራርተዋል።

የማህበረሰቡን ተሳትፎ በማጎልበት መድሃኒት የተላመደ የቲቢ በሽታን በመቆጣጠር ረገድ የተገኘው ውጤት አበረታች መሆኑንም ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ የቲቢ በሽታ ስርጭት በከፍተኛ ደረጃ ከሚገኝባቸው 30 ሀገሮች ዝርዝር ውስጥ መውጣቷንም አስታውቀዋል።

ውጤቱ የተገኘውም የህብረተሰቡን ንቃተ ጤና በማጎልበትና በማሳተፍ በተከናውኑ ስራዎች በመሆኑ የተገኘው ውጤት ቀጣይነት እንዲኖረው በሁሉም መዋቅሮች አጠናክሮ መስራት እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል።

የጤና ሚኒስቴር የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክተር ወ/ሮ ሕይወት ሰለሞን በበኩላቸው ፥ በቀጣይ መድሃኒት የተላመደ ቲቢ ልየታና ህክምና በመተግበር ያልደረስንባቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች መድረስና ማከም አለብን ብለዋል።

አክለውም የበሽታውን ስርጭት በመቀነስና በመቆጣጠር በዓለም አቀፍ ደረጃ የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት መስራት ይጠበቅብናል ነው ያሉት።

በግምገማው ላይ የክልሎች ጤና ቢሮ ኃላፊዎችና ተወካዮች፣ የቲቢና ሥጋ ደዌ በሽታ አስተባባሪዎች፣ አጋር ድርጅቶች፣ የተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶችና የሙያ ማህበራት መሳተፋቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.