Fana: At a Speed of Life!

ቱርክና ሶሪያ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሩስያ አግባቢነት ቱርክና ሶሪያ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ፡፡

ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ብቻ የቱርክ የደህንነት ተቋም ኃላፊ የሆኑት ሃካን ፊዳን ከሶሪያ አቻቸው አሊ ማምሉክ ጋር በደማስቆ ለበርካታ ጊዜ መገናኘታቸው እና መምከራቸውም ተነግሯል፡፡

ይህም ሩሲያ በሁለቱ የማይግባቡ ሀገራት መካከል ስምምነት ለማስፈን የምታደርገው ጥረት ውጤት መሆኑን የዜና ምንጮች ዘግበዋል፡፡

ሩሲያ እንደ ባላንጣ ይተያዩ በነበሩ ሀገራት መካከል ሠላም ለማስፈን እየጣረች ያለችው አጸፋውን ከሶሪያ በመሻት እንደሆነም እየተነገረ ነው፡፡

እንደሚታወቀው ሩሲያ ከዩክሬን ጋር የተራዘመ ግጭት ውስጥ ገብታለች፡፡

በመሆኑም ሩሲያ ከፈረንጆቹ 2015 ጀምሮ በወታደራዊ ኃይል ስታግዛት ከቆየችው ከሶሪያ አሁን ላይ “የቁርጥ ቀን የወዳጅነት ድጋፍ” ትሻለች መባሉን አልአራቢያ ኒውስ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.