ፋሲል ከነማ ከብሩንዲው ቡማሙሩ ክለብ ጋር የመልስ ጨዋታውን ዛሬ ያደርጋል
አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፋሲል ከነማ ከብሩንዲው ቡማሙሩ ክለብ ጋር የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የቅድመ-ማጣሪያ የመልስ ጨዋታውን ዛሬ ያደርጋል፡፡
የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ከቀኑ 10 ሰአት ላይ 10 ሺህ ተመልካች በሚያስተናግደው የታንዛንያው አዛም ኮምፕሌክስ ስታዲየም ይከናወናል።
ጨዋታው በታንዛንያ የሚደረገው ቡማመሩ የሚጫወትበት ስታዲየም የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ)ን መስፈርት ባለሟሟላቱ ምክንያት መታገዱን ተከትሎ ነው።
የአሰልጣኝ ሀይሉ ነጋሽ ቡድን በባህርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ባደረገው የመጀመሪያ ጨዋታ ተጋጣሚውን 3 ለ 0 ማሸነፉን ተከትሎ ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ እድሉን በማስፋት ወደ ሜዳ ይገባል፡፡