ስፓርት

ፋሲል ከነማ በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ የመጀመሪያ የቅድመ ማጣሪያ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፈ

By Feven Bishaw

September 16, 2022

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 6 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ የመጀመሪያ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ከቡሩንዲው ቡማሙሩ ጋር የተጫወተው ፋሲል ከነማ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፉን አረጋግጧል።

ፋሲል ከነማ በዛሬው እለት በመልስ ጨዋታው 1 ለ 0 ቢሸነፍም በድምር 3ለ1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፏል።