Fana: At a Speed of Life!

የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸው መድሀኒቶች እና ሌሎች የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

 

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 6 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ25 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸው መድሀኒቶች እና ሌሎች የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸውን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ።

 

ሀሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀት እና ኮንቴነሮችን በሀሠተኛ ማሸጊያ በማሸግ ወደ መሀል ሀገር ሊገቡ የነበሩት መድሀኒቶችን ሌሎች እቃዎች 25 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር ግምታዊ ዋጋ እንዳላቸውም ነው ያስታወቀው።

 

በአዋሽ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ቤት የተያዙት መጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው መድሀኒቶች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ አልባሳት፣ ሽቶዎች እና የመዋቢያ እቃዎች መሆናቸውንም ገልጿል።

 

የኮንትሮባንድ በአካባቢው ማህበረሰብ ፣ በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች እና አመራሮች እንዲሁም የጸጥታ አካላት በሰሩት የተቀናጀ ስራ መያዛቸውም ታውቋል።

 

በዚህ ስራ ተሳትፎ ለነበራቸው አካላትም ኮሚሽኑ ምስጋናውን አቅርቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.