Fana: At a Speed of Life!

ጅማ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 476 ተማሪዎች አስመረቀ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 7 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጅማ ዩኒቨርሲቲ በጤና እና በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 476 ተማሪዎች አስመረቀ።

ጅማ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ ዲግሪ 308 ተማሪዎችን እንዲሁም በድህረ ምረቃው 168 ተማሪዎችን አስመርቋል።

ከተመራቂዎቹ መካከል አራቱ በዶክትሬት ዲግሪ እንዲሁም ስምንቱ በክሊኒካል ስፔሻሊቲ የተመረቁ ናቸው ተብሏል።

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ጀማል አባፊጣ፥ ሀገራችን በበርካታ ችግሮች ውስጥ ባለችበት በዚህ ወቅት የተመረቁ ተማሪዎች ማህበረሰቡን የማገልገል ከፍተኛ ሀላፊነት እንዳለበቸው ተናግረዋል።

በዛሬው እለት የተመረቁ አብዛኛዎቹ የጤና ምሩቃን በመሆናቸው የቀሰሙትን እውቀት ወገናቸውን በትዕግስት ለመርዳት እንዲጠቀሙበት መልክታቸውን አስተላልፈዋል።

በወርቅአፈራው ያለው እና በሙክታር ጣሀ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.