Fana: At a Speed of Life!

ጣሊያን ለኃይል ዘርፍ 14 ቢሊየን ዶላር የእርዳታ ማዕቀፍ አፀደቀች

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 7 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጣሊያን ለኃይል ዘርፍ የሚውል 14 ቢሊየን ዶላር የእርዳታ ማዕቀፍ ማጽደቋን አስታወቀች።

አሁን የጸደቀው ማዕቀፍ በሀገሪቱ በኃይል አቅርቦት ክፍያ ያጋጠመውን የዋጋ ማሻቀብ ለማስተካከል ያለመ መሆኑን ተገልጿል።

ማዕቀፉ የግብር እፎይታን ጨምሮ፥ የግብር ቅነሳ፣ የተለያዩ ማበረታቻዎች እና ድጎማዎችን ያካተተ ነው ተብሏል።

ከሩሲያ ዩክሬን ግጭት ጋር ተያይዞ በአውሮፓ ሀገራት የኃይል አቅርቦት ዋጋ በእጅጉ መጨመሩ ይነገራል።

የዚህ ችግር ሰለባ የሆነችው ጣሊያንም ይህን ችግር ለማስተካከል ማዕቀፉን ማፅደቅ እንዳስፈለጋት ጠቅላይ ሚኒስትር ማሪዮ ድራጊ ተናግረዋል።

በማዕቀፉ መሰረት ኃይል አቅራቢ ኩባንያዎቹ ከ15 እስከ 25 በመቶ የሚደርስ የግብር ቅናሽ እስከ መስከረም 30 የሚደረግላቸው ሲሆን፥ በቀጣዩ ወርም እስከ 40 በመቶ የሚደርስ ቅናሽ ይደረግላቸዋል።

ከዚህ ባለፈም በናፍጣ እና ቤንዚን ላይ የተጣለው የኤክሳይዝ ታክስ ከህዳር ወር ጀምሮ ቅናሽ ይደረግበታል ነው የተባለው።

በተጨማሪም ለዜጎች የሚደረግ የአንድ ጊዜ የድጎማ ክፍያን ጨምሮ ለኃይል ክፍያ ከፍተኛ ገንዘብ የሚያወጡ አርሶ አደሮችን መደጎም የሚያስችል አሰራሮችን ያካተተ መሆኑን ሺንዋ በዘገባው አመላክቷል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.