Fana: At a Speed of Life!

የነገ ተስፋ ለሆነው የህዳሴ ግድብ ኢትዮጵያውያን ድጋፋቸውን እንዲያጠናክሩ የሃይማኖት አባቶች ጠየቁ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ታላቁ የህዳሴ ግድብ የሁላችንም የጋራ ሃብትና የነገ ተስፋ በመሆኑ ኢትዮጵያውያን ሰላምና አንድነታቸውን በማስጠበቅ ለግድቡ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ሲሉ የሃይማኖት አባቶች ጠየቁ፡፡

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች የግድብን የግንባታ ሂደትና አሁናዊ ሁኔታ ጎብኝተዋል።

ለኢትዮጵያና ለግድቡ ሠራተኞች በስፍራው ፀሎት በማድረግም ግድቡን ባርከዋል።

አባቶች ሦስተኛው ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት በመጠናቀቁና አሁን ለደረሰበት ደረጃ ለኢትዮጵያውያን እንኳን ደስአላችሁ ብለዋል፡፡

የጉባኤው ጠቅላይ ፀሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ፥ ለአገር ብልጽግና፣ ልማትና አንድነት ምሳሌ የሆነውን ግድብ ከዳር ለማድረስ ጥረት ማድረግ አለብን ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.