በሲድኒ የሴቶች ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸነፉ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአውስትራሊያ ሲድኒ በተደረገ የሴቶች ማራቶን ውድድር ኢትዮጵውያን አትሌቶች በፍጽም የበላይነት አሸንፈዋል፡፡
አትሌት ትዕግስት ግርማ ርቀቱን 2 ሰዓት 25 ደቂቃ ከ10 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በመጨረስ ወድድሩን በአንደኛነት አጠናቃለች፡፡
ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ለተብርሃን ሀይላይ ርቀቱን 2 ሰዓት ከ25 ደቂቃ 45 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በመጨረስ ሁለተኛ ስትሆን ÷ኤርትራዊቷ ናዝሬት ወልዱ ደግሞ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች።
በውድድሩ ኢትዮጵያውን አትሌቶች ከ1 እስከ 2 እና ከ4 እስከ 6 ያለውን ደረጃ በመያዝ ነው በፍጹም የበላይነት ያሸነፉት፡፡
በተመሳሳይ በወንዶች የሲድኒ ማራቶን ደግሞ ኢትዮጵያዊው አትሌት ጫሉ ዲሶ ርቀቱን 2 ሰዓት ከ07 ደቂቃ ከ09 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በመግባት ሦስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል፡፡
እጅግ ከባድ ፉክክር በታየበት በሲድኒ የወንዶች ማራቶንን ኬንያዊው ሞሰስ ኪቤት ማሸነፉን ከሲድኒ ኦሎምፒክ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡