ስፓርት

በሲድኒ  የሴቶች ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸነፉ

By Mikias Ayele

September 18, 2022

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአውስትራሊያ ሲድኒ በተደረገ የሴቶች ማራቶን ውድድር ኢትዮጵውያን አትሌቶች በፍጽም የበላይነት አሸንፈዋል፡፡

አትሌት ትዕግስት ግርማ ርቀቱን 2 ሰዓት 25 ደቂቃ ከ10 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በመጨረስ  ወድድሩን በአንደኛነት አጠናቃለች፡፡

ሌላኛው ኢትዮጵያዊ  አትሌት  ለተብርሃን ሀይላይ ርቀቱን  2 ሰዓት ከ25 ደቂቃ 45 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በመጨረስ ሁለተኛ ስትሆን ÷ኤርትራዊቷ ናዝሬት ወልዱ ደግሞ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች።

በውድድሩ ኢትዮጵያውን አትሌቶች ከ1 እስከ 2 እና ከ4 እስከ 6 ያለውን ደረጃ በመያዝ ነው በፍጹም የበላይነት ያሸነፉት፡፡

በተመሳሳይ በወንዶች የሲድኒ ማራቶን ደግሞ ኢትዮጵያዊው አትሌት ጫሉ ዲሶ  ርቀቱን 2 ሰዓት ከ07 ደቂቃ ከ09 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በመግባት ሦስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል፡፡

እጅግ ከባድ ፉክክር በታየበት በሲድኒ የወንዶች ማራቶንን ኬንያዊው ሞሰስ ኪቤት ማሸነፉን ከሲድኒ ኦሎምፒክ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡