Fana: At a Speed of Life!

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ወርቅ በሚመረተው ልክ ወደ ብሔራዊ ባንክ እየገባ አይደለም ተባለ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ወርቅ በሚመረተው ልክ ወደ ብሔራዊ ባንክ እየገባ አለመሆኑ ተገለጸ፡፡

በዘርፉ ላይ እየታየ ያለውን ችግር ለመፍታት እና የአሠራር የእርምት እርምጃዎች ለመውሰድ የሚስችል ውይይት በአሶሳ ከተማ ተካሂዷል፡፡

የማዕድን ሚኒስትር ታከለ ዑማ በውይይቱ ላይ እንደገለጹት÷ ወርቁ ወደ ብሔራዊ ባንክ የማይገባው ስለማይመረት ሳይሆን በሕገወጥ መንገድ ከሀገር እየወጣ እና ከፍተኛ የሆነ አሻጥር እየተፈፀመበት በመሆኑ ነው።

ስለሆነም የእርምት እርምጃ በመውሰድ ሀገር የሚገባትን እንድታገኝ ማድረግ ግዴታ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን በበኩላቸው÷ በ2014 ዓ.ም 23 ኩንታል ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ መግባቱን ገልፀው በዓመቱ መጨረሻ ሐምሌና ነሐሴ ወር ከፍተኛ የምርት መቀነስ መታየቱን አብራርተዋል፡፡

በዚህም በክልሉ በሐምሌና ነሐሴ ወር 317 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ለማስገባት ታቅዶ 110 ኪሎ ግራም ብቻ ማሳካት መቻሉን ገልጸዋል፡፡

ከ2013 ዓ.ም ተመሳሳይ ሁለት ወራት ጋር ሲነፃፀር ከ200 ኪሎ ግራም በላይ ምርቱ ቀንሷል ነው የተባለው።

መድረኩ በኩባንያም ሆነ በልዩ አነስተኛ ወርቅ አምራቾች ፣ በወርቅ አዘዋዋሪዎች እና በዘርፉ ተዋናዮች በኩል የሚታየውን ችግር በዝርዝር በመለየት የመፍትሄ አቅጣጫ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ተጠናቋል፡፡

በመታገስ አየልኝ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.