ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ በንግስት ኤልሳቤጥ ሁለተኛ የቀብር ስነ ስርዓት ላይ ተገኙ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ በንግሊዟ ንግስት ኤልሳቤጥ ሁለተኛ የቀብር ስነ ስርዓት ላይ ተገኝተዋል።
ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ በትናንትናው ዕለት በንግስት ኤልሳቤጥ ህልፈት የተሰማቸውን ሐዘን ለንደን በመገኘት መግለጻቸው ይታወሳል፡፡
በዛሬው ዕለትም የበርካታ ሀገራት ርዕሰ ብሄሮች፣ መሪዎች እና የንጉሣውያን ቤተሰቦች በተገኙበት የንግስቷ የቀብር ስነስርዓት ላይ ተገኝተዋል።
ለ70 ዓመት እንግሊዝን በንግስትነት ያገለገሉት ንግስት ኤልሳቤጥ በ96 ዓመታቸው ከሳምንት በፊት ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ይታወሳል።