Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ ማዳበሪያ በነጻ ለአፍሪካ ልታቀርብ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ ታዳጊ ለሆኑ የአፍሪካ ሀገራት በሺህ ቶኖች የሚቆጠር ማዳበሪያ በነጻ ልታቀርብ መሆኑ ተሰምቷል፡፡

የሩሲያ የማዕድንና የፖታሽ ማዳበሪያዎች አምራች ዩራልቼም ፥ ምርቶቹን ለአፍሪካ በነጻ ለማቅረብ መወሰኑን የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ዲሚትሪ ኮኒያዬቭ አስታውቀዋል፡፡

በዚህም የመጀመሪያውን 25 ሺህ ቶን ማዳበሪያ ወደ ቶጎ እንደሚላክም ነው የተገለጸው፡፡

የኩባንያው ዋና ስራ አስፈጻሚ ፥ ሀገሪቱ ማዳበሪያ መስጠቷና ወደ ውጭ መላኳ በምግብ ዋስትናዋ ላይ አንዳች ችግር አይፈጥርም ሲሉ ነው የገለጹት፡፡

በዚህ ወር መጀመሪያ የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በሻንጋይ የትብብር ድርጅት የመሪዎች ስብሰባ ላይ፥ በምዕራቡ ዓለም በተጣለባት ማዕቀብ ሳቢያ በወደቦች የተጠራቀመ 300 ሺህ ቶን ማዳበሪያን ለታዳጊ ሀገራት በነፃ ታቀርባለች ማለታቸው ይታወሳል።

ፑቲን ሩሲያ የማዳበሪያ ምርቷን ወደ አውሮፓ ህብረት ለመላክ የሚያስችለውን ውሳኔ በደስታ ቢቀበሉም፥ የህብረቱ አባል ሀገራት ብቻ እንዲገዙ የቀረበውን ሀሳብ መተቸታቸውን የዘገበው አር ቲ ነው፡፡

በሐምሌ ወር መጨረሻ ሞስኮና ኪየቭ በኢስታንቡል በተመድ አደራዳሪነት ባደረጉት ውይይት በጥቁር ባህር በኩል ዩክሬን የእህል ምርቶቿን ለዓለም ገበያ እንድታቀርብ መስማማታቸው የሚታወስ ነው።

ስምምነቱ ሩሲያ የማዳበሪያና የምግብ ሸቀጦችን ለዓለም አቀፉ ገበያ እንድታቀርብ የሚፈቅድ ቢሆንም ሞስኮ ግን ይህ ተፈጻሚ አለመሆኑን ገልጻለች።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.