የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ተቋቋመ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል እንዲቋቋም የቀረበው ምክረ ሃሳብ ተቀባይነት ማግኘቱ ተገለጸ።
በዛሬው ዕለት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ካውንስሉ የወንጌላውያን አማኞች አብያተ ክርስቲያናትን መብት እና ግዴታ ለማስከበር ያስችላል ተብሏል።
ከዚህ ባለፈም ካውንስሉ የወንጌላውያን አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ተቀራርበውና ተባብረው ያለባቸውን ሃገራዊ ግዴታ ለመወጣት ያስችላል ነው የተባለው።
በአብያተ ክርስቲያናቱ መካከል የተነሱ ልዩ ልዩ የአስተምህሮ፣ ስነ ምግባር፣ አስተዳደራዊና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን በጋራ ምክክር ለመፍታት እንደሚያስችል የካውንስሉ ሰብሳቢ ቄስ ደረጀ ጀምበሩ ተናግረዋል።
በሌላ በኩል በሃገሪቱ የተከሰተውን የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል ህዝበ ክርስቲያኑ እና ምእመኑ በጸሎት ቦታዎች ቁጥሩን ሊቀንስ እና የጤና ባለሙያዎችን ትዕዛዝ ሊተግርብር እንደሚገባም መልእክት ተላልፏል።
በይስማው አደራው
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision