Fana: At a Speed of Life!

የሐረሪ ክልል ካቢኔ ለከተማ ተቋማዊና መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም ከ203 ሚሊየን ብር በላይ በጀት አፀደቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በከተማ ተቋማዊና መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም ለሚከናወኑ ፕሮጀክቶች ማስፈፀሚያ ከ203 ሚሊየን ብር በላይ በጀት አፅደቀ።

ካቢኔው በከተማ ተቋማዊና መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎችን ገምግሟል።

የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት፥ ባካሄደው ስብሰባ በክልሉ በፕሮግራሙ በ2014 የበጀት አመት የተከናወኑ ተግባራትን በመገምገም የ2015 የበጀት ዓመት ካፒታል ኢንቨስትመንት እቅድን መርምሮ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።

በሐረር ማዘጋጃ ቤት የከተማ ተቋማዊና የመሠረተ ልማት ልማት መርሐ ግብር ማሰተባበሪያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፈቲህ ረመዳን የ2014 የበጀት ዓመት ስራ አፈፃፀም ሪፖርትና የ2015 የበጀት ዓመት እቅድ ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።

ከፀደቀው ከ203 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር በላይ በፕሮግራሙ ተጀምረው ላልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች የሚውል መሆኑም ተገልጿል።

የካቢኔ አባላትም ፕሮጀክቶች በታቀደላቸው የጊዜ ገደብና ጥራት እንዲጠናቀቁ በትኩረት እንዲሰራ አቅጣጫ ማስቀመጣቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.