Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ክልል ፖሊስ በተለያዩ ወንጀሎች ጠረጠርኩት ያለውን ዘመነ ካሴን በቁጥጥር ስር አዋለ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የአማራ ክልል ፖሊስ በተለያዩ ወንጀሎች ጠረጠርኩት ያለውን ዘመነ ካሴን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ፡፡

ግለሰቡ በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 3 በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ተደብቆ በህብረተሰቡ ጥቆማ መያዙን የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን የታክቲክ ወንጀል ምርመራ ምክትል ዘረፍ ሃላፊ ኮማንደር ክንዱ ወንዴ ገልፀዋል፡፡

በወቅቱ ከ500 ሺህ ብር በላይ በኢግዚቢት መያዙ የተገለፀ ሲሆን÷ ቀሪ የምርመራና የፍተሻ ሂደቶች እየተከወኑ መሆኑን ኮማንደሩ መናገራቸውን ከአማራ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.