የሀገር ውስጥ ዜና

የአማራ ክልል ፖሊስ በተለያዩ ወንጀሎች ጠረጠርኩት ያለውን ዘመነ ካሴን በቁጥጥር ስር አዋለ

By Feven Bishaw

September 21, 2022

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የአማራ ክልል ፖሊስ በተለያዩ ወንጀሎች ጠረጠርኩት ያለውን ዘመነ ካሴን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ፡፡

ግለሰቡ በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 3 በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ተደብቆ በህብረተሰቡ ጥቆማ መያዙን የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን የታክቲክ ወንጀል ምርመራ ምክትል ዘረፍ ሃላፊ ኮማንደር ክንዱ ወንዴ ገልፀዋል፡፡