Fana: At a Speed of Life!

በሶማሌ ክልል በሰብል ለመሸፈን በታቀደው እቅድ መሰረት አበረታች ውጤት እየተመዘገበ  ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዘንድሮ በጀት አመት በአጠቃላይ በክልሉ  847 ሺህ ሄክታር መሬት በሰብል ለመሸፈን በታቀደው እቅድ አበረታች ውጤት እየተመዘገበ መሆኑ ተገለፀ።

በሶማሌ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳደር  ኢብራሂም ኡስማን የተመራ የክልሉ ከፍተኛ አመራር ልዑክ በፋፈን ዞን አውባሬና ቱሊ-ጉሌድ ወረዳ የለማ የስንዴ ማሳዎችን ጎበኘ፡፡

በመስክ ምልከታው  ምክትል ርእሰ መስተዳድሩ÷  በዘንድሮ በጀት አመት በአጠቃላይ የክልሉ አከባቢዎች 847 ሺህ ሄክታር መሬት በሰብል ለመሸፈን በታቀደው እቅድ መሰረት አበረታች ውጤት እየመጣ ነው ብለዋል።

በአውባሬና በቱሊ ጉሌድ  ወረዳዎች ላይ የተዘጋጀው የእርሻ መሬት በጥሩ ሁኔታ እየታረሰ መሆኑንም ገልጸው ህዝቡ የመሬት ሀብታቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙና የተጀመረውን የግብርና ምርት ምርታማነትን እንዲቀጥሉ አሳስበዋል።

የሶማሌ ክልል ግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ኃላፊ አብዲቃድር ኢማን በበኩላቸው÷ በፋፈን ዞን የአውባሬ ወረዳ ቆላማ አከባቢዎች 42ሺህ ሄክታር መሬት በስንዴ ሰብል ለመሸፈን  መታቀዱን ተናግረዋል፡፡

በቱሊ ጉሌድ ወረዳ ደግሞ 62ሺህ ሄክታር መሬት በስንዴ ምርት እንደሚሸፈንና በአጠቃላይ በሁለቱ ወረዳዎች 104 ሺህ ሄክታር መሬት በስንዴ ለመሸፈን መታቀዱን መግለፃቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.