Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ባጫ ደበሌ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ መንግስት እያደረገ ያለውን የሰላም ጥረት እንዲደግፍ ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 12 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ባጫ ደበሌ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የኢትዮጵያ መንግስት እያደረገ ያለውን የሰላም ጥረት እንዲደግፍ ጥሪ አቀረቡ።
 
አምባሳደር ባጫ በኬንያ ለተባበሩት መንግስታት ፅህፈት ቤት ሃላፊ ዘይነብ ሃዋ ባንጉራ በፅህፈት ቤቱ ቋሙ መልዕክተኛ ሆነው የተሾሙበትን ደብዳቤ አቅርበዋል።
 
በዚህ ወቅትም ኢትዮጵያ በተመድ ያላትን ወሳኝ ሚና እና በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለፅህፈት ቤት ሃላፊዋ ገለጻ አድርገዋል።
 
አምባሳደር ባጫ መንግስት ኢትዮጵያ ከተመድ ጋር በአየር ንብረት ለውጥ፣ በከተሞች ልማት እና ዓለም አቀፍ ፀጥታና ደህንነት ያላትን ዘርፈ ብዙ ትብብር አጠናክሮ ለመቀጠል ፅኑ ፍላጎት እንዳለው ገልጸዋል።
 
አያይዘውም ኢትዮጵያ ተመድ በሚያከናውናቸው የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች ከፍተኛ ሰራዊት ከሚያሰልፉ አምስት ሀገራት አንዷ ናት ብለዋል።
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.