Fana: At a Speed of Life!

ምዕራባውያኑ ሩሲያን መበታተን ይፈልጋሉ – ፕሬዚዳንት ፑቲን

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 12 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምዕራባውያኑ ሩሲያን የመበታተን ሐሳብ እንዳላቸው የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን አስታወቁ፡፡

ቭላድሚር ፑቲን እንዳሉት በአሁኑ ሰዓት ሀገራቸው በምዕራባውያኑ ጥቃት እየደረሰባት ነው፡፡

ዓላማቸውም የሀገራቸውን አንድነት ማላላት እና እንደ ሀገር እንዳትቀጥል መበተን መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ምዕራባውያኑ በፈረንጆቹ 1991 ሶቪየት ኅብረትን ለመበታተን እንደሰሩ ራሳቸው መግለጻቸውንም አንስተዋል።

ቭላድሚር ፑቲን በቴሌቪዥን ባስተላለፉት መልዕክት አሁን ላይ ምዕራባውያኑ እንደቀድሞው ሁሉ ሩሲያን ወደ በርካታ ክልሎች ለመከፋፈል እና አንዱ ክልል በአንዱ ላይ እንዲነሳ ለማድረግ እየሠሩ ነው ብለዋል፡፡

ፑቲን ጉዳዩን የገለጹት የሩሲያ ወታደራዊ ኃይል በዩክሬን በሚያደርገው ዘመቻ ላይ አዲስ ማብራሪያ በሰጡበት እና ለተጠባባቂ የሩሲያ ወታደራዊ ሠራዊት ጥሪ ባቀረቡበት ወቅት መሆኑንም አር ቲ ዘግቧል፡፡

የአሁኑ የሩሲያ-ዩክሬን ግጭት ምዕራባውኑ ሩሲያ ላይ ባላቸው ጥላቻ የተፈጠረ መሆኑን አስምረውበታል፡፡

የአሜሪካ እና አጋሮቿ ግብም በጦርነቱ ሩሲያ እንድትሸነፍ መሥራትና የሀገሪቷን ሉዓላዊነት እንዲሁም ፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊ እና ባሕላዊ ዕሴት ማጥፋት መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.