Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ እና ዩክሬን የምርኮኛ ልውውጥ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ እና ዩክሬን 300 የሚጠጉ የጦር ምርኮኞች ልውውጥ አድርገዋል፡፡

በልውውጡ ከተካተቱት ምርኮኞች ውስጥ 10 ለዩክሬን ተሰልፈው ሲዋጉ የነበሩ የሌላ ሀገር ወታደሮች እና የዩክሬን ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች ይገኙበታል ነው የተባለው፡፡

ሩሲያ ከለቀቀቻቸው የጦር ምርኮኞች መካከል የአሜሪካ፣ እንግሊዝ  እና የሞሮኮ ዜግነት ላቸው የጦር እስረኞች ሲገኙ፥ ዩክሬን በበኩሏ እየተካሄደ በነበረው ጦርነት የሞት ፍርድ የፈረደችባቸውን ቅጥረኛ ሰራዊቶች መልቀቋ ተሰምቷል፡፡

በልውውጡ ሩሲያ የማሪዮፑልን ጦርነት የመሩ አምስት የዩክሬን ወታደራዊ አዛዦች ጨምሮ 215 የጦር ምርኮኞችን ስትለቅ በምትኩ ዩክሬን 55 ሩሲያውያንን እና የሞስኮ ደጋፊ የሆኑ ዩክሬናውያንን ለቃለች፡፡

የምርኮኛ ልውውጡ በቱርክ እና በሳዑዲ አረቢያ አሸማጋይነት የተደረገ ሲሆን የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቭሎዶሚር ዜለንስኪ ሀገራቱ ላደረጉት የአደራዳሪነት ሚና ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የእንግሊዟ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዝ ትሩስ በትዊተር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት በምርኮኛ ልውውጡ  በሩሲያ ተማርከው የነበሩ የእንግሊዝ ወዶ ዘማቾች መለቀቃቸውን አስታውቀዋል፡፡

የምርኮኛ ልውውጡ እንዲሳካ ለተባበሩት ቭሎዶሚር ዜለንስኪ፣ሳዑዲ አረቢያ እና ቱርክ ጠቅላይ ሚኒስትሯ ምስጋና ማቅረባቸውን አር ቲ ነው የዘገበው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.